ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'"
ከፍ ያለውና የላቀው አላህ "የአደም ልጅ ሆይ! ግዴታም ይሁን ተወዳጅ የሆኑብህን ወጪዎች ለግስ! ላንተም ሲሳይን አሰፋልሃለሁ፣ ያዋጣኸውን ወጪ ልውጫ እሰጥሃለሁ፣ በሰጠሁህም ነገር ላንተ እባርክልሃለሁ" ማለቱን ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም...
ከአቡ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው (ምንዳ እንደሚያገኝበት) እያሰበ ለቤተሰቡ ወጪ ያወጣ ጊዜ ለርሱ ምፅዋት ትሆንለታለች።"
ሰውዬው እንደሚስቱ፣ ወላጆቹ፣ ልጁና ሌሎችንም እነርሱ ላይ ወጪ ማውጣት ግዴታ ለሆነበት አካል ሲሰጥ ወደ አላህ መቃረብንና አላህ ዘንድ ምንዳን እያሰበ ከሆነ ለርሱ የምፅዋት ምንዳ እንደሚሰጠው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ...
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሞተ ሰው በመሞቱ ስራው እንደሚቋረጥ፤ ከነዚህ ሶስት ስራዎች ውጪም ከሞተ በኋላ ምንዳ የሚያገኝበት እንደሌለው ተናገሩ። ሶስቱ ስራዎች ግን ሰበባቸው እርሱ ስ...
ከማሊክ ቢን አውስ ቢን ሐደሣን እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዲርሃም የሚመነዝርልኝ እያልኩኝ ተዘዋወርኩኝ። ጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ዘንድ እያለ እንዲህ አለኝ:...
ታቢዒዩ ማሊክ ቢን አውስ እርሱ ዘንድ በብር ዲርሃም ሊመነዝራቸው የፈለጋቸው የወርቅ ዲናሮች እንደነበሩት ተናገረ። ጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ለርሱ "ዲናርህን አምጣና እንየው።" አ...
ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ይስፈንና ዘካተል ፊጥርን አንድ ቁና ከተምር ወይም አንድ ቁና ከገብስ ማውጣትን...
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከረመዷን በኋላ ዘካተል ፊጥርን ግዴታ አደረጉ። መጠኑም አራት እፍኝ የሚያህል አንድ ቁና ነው። አንድ እፍኝ፡ ማለት የመካከለኛ ሰው መዳፍ የሚሞላ ነው። ግዴታ ያደረጉትም ሁሉም ነፃ፣...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'"

ከአቡ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው (ምንዳ እንደሚያገኝበት) እያሰበ ለቤተሰቡ ወጪ ያወጣ ጊዜ ለርሱ ምፅዋት ትሆንለታለች።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው ሲቀር ሌሎቹ ስራዎቹ ይቋረጣሉ።"

ከማሊክ ቢን አውስ ቢን ሐደሣን እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዲርሃም የሚመነዝርልኝ እያልኩኝ ተዘዋወርኩኝ። ጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ዘንድ እያለ እንዲህ አለኝ: "ወርቅህን አሳየንና ከዚያም ተመልሰህ ና! አገልጋያችን የመጣ ጊዜ ገንዘብህን እንሰጥሃለን።" በዚህ ጊዜ ዑመር ቢን ኸጧብ እንዲህ አለ: "በፍፁም! በአላህ እምላለሁ! ወይ አሁን ብሩን ትሰጠዋለህ ወይም ወርቁን ትመልስለታለህ! የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ብር በወርቅ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ስንዴ በስንዴ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ገብስ በገብስ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ተምር በተምር መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው።›"»

ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ይስፈንና ዘካተል ፊጥርን አንድ ቁና ከተምር ወይም አንድ ቁና ከገብስ ማውጣትን በባሪያውም፣ በነፃውም፣ በወንዱም፣ በሴቱም፣ በህፃኑም፣ በትልቁም ሙስሊም ላይ ግዴታ አደረጉ። ሰዎች ወደ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"

ከዐብደላህ ቢን ሰላም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መዲና የገቡ ጊዜ ሰዎች ወደርሳቸው በፍጥነት ሄዱ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ ‐ ሶስት ጊዜ ‐ እየተባለ ተወራ። ለመመልከትም ከሆኑ ሰዎች ጋር መጣሁ። ፊታቸውን የተመለከትኩኝ ጊዜ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቅኩ። መጀመሪያ ሲናገሩ የሰማሁት ነገር እንዲህ ሲሉ ነው: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ ጀነት ትገባላችሁ በሰላም።"»

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ መልካም (ጥሩ) ነውና ከመልካም (ከጥሩ) በቀር አይቀበልም። አላህ መልክተኞችን ባዘዘው ነገር አማኞችንም አዟል። አላህ እንዲህ ብሏል: {እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ስራንም ስሩ። እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝ።} [አልሙእሚኑን:51] እንዲህም ብሏል: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮችን ብሉ።} [አልበቀራህ: 172]" ቀጥለውም ጉዞ የሚያረዝም፣ ጨብራራ፣ ፊቱንና ልብሱን አቧራ ያለበሰው አንድ ሰውዬ አወሱ። እጁን ወደ ሰማይ እየዘረጋ: "ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! እያለ ይለምናል። ምግቡ ሐራም ነው። መጠጡ ሐራም ነው። ልብሱ ሐራም ነው። በሐራም ነው የተገነባው። እንዴት ለርሱ ዱዓው ተቀባይነት ይኖረዋል?" አሉ።»

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።"

ከጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።"

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን የተቸገረ ካጋጠመህ እለፈው።' (ሞተና) አላህንም ተገናኘ፤ አላህም ይቅር አለው።"

ከኸውለህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።› ፆም ጋሻ ነው። አንዳችሁ የፆም ቀኑ የሆነ ጊዜ ፀያፍ ቃልንም አይናገር አይጩህም። አንድ ሰው ከተሰዳደበው ወይም ከተጋደለው እኔ ፆመኛ ሰው ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የፆመኛ ሰው የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽታ የበለጠ ታውዳለች። ፆመኛ የሚደስትባቸው ሁለት ደስታ አሉት። ሲያፈጥርም ይደሰታል። ጌታውን የተገናኘ ጊዜም በመፆሙ ይደሰታል።"»