/ ሰውዬው (ምንዳ እንደሚያገኝበት) እያሰበ ለቤተሰቡ ወጪ ያወጣ ጊዜ ለርሱ ምፅዋት ትሆንለታለች።

ሰውዬው (ምንዳ እንደሚያገኝበት) እያሰበ ለቤተሰቡ ወጪ ያወጣ ጊዜ ለርሱ ምፅዋት ትሆንለታለች።

ከአቡ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው (ምንዳ እንደሚያገኝበት) እያሰበ ለቤተሰቡ ወጪ ያወጣ ጊዜ ለርሱ ምፅዋት ትሆንለታለች።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ሰውዬው እንደሚስቱ፣ ወላጆቹ፣ ልጁና ሌሎችንም እነርሱ ላይ ወጪ ማውጣት ግዴታ ለሆነበት አካል ሲሰጥ ወደ አላህ መቃረብንና አላህ ዘንድ ምንዳን እያሰበ ከሆነ ለርሱ የምፅዋት ምንዳ እንደሚሰጠው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

Hadeeth benefits

  1. ለቤተሰቦች ወጪ በማውጣት ምንዳና አጅር እንደሚገኝ እንረዳለን።
  2. ሙእሚን የሆነ ሰው በስራው የአላህን ፊትና እርሱ ዘንድ ያለውን ምንዳና አጅር እንደሚፈልግ እንረዳለን።
  3. በሁሉም ስራዎች መልካምን ኒያ ማድረግ ይገባል። ከነዚህም ስራዎች መካከል ለቤተሰቦች ወጪ በምናወጣ ጊዜ አንዱ ነው።