- የሰው ልጅ ከሞተ በኋላ የሚደርሰው ምንዳ ተሻጋሪ ምፅዋት፣ በርሱ ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት ያስተላለፈ እና ዱዓ እንደሆነ የእውቀት ባለቤቶች ባጠቃላይ ተስማምተዋል። ልክ እንደዚሁ ሐጅም ከሞተ በኋላ እንደሚደርሰው በሌላ ሐዲሥ መጥቷል።
- ሐዲሡ ውስጥ ሶስቱ ብቻ የተጠቀሱት ሶስቱም የመልካም ስራ መሰረቶች ስለሆኑ እና አብዛኛው ጊዜ ባለፀጋዎቹ ከነርሱ ህልፈት በኋላ ይቀራሉ ብለው የሚያስቧቸው እነዚህን ስለሆነ ነው።
- ማንኛውም ሰዎች በርሱ የሚጠቀሙበት እውቀት ምንዳ ይገኝበታል። ነገር ግን ዋናውና ቁንጮው ሸሪዓዊ እውቀትና የሸሪዓን እውቀት ለመረዳት የሚያግዙ እውቀቶች ናቸው።
- እውቀት ከሶስቱም እጅግ ጠቃሚው ነው። ምክንያቱም በእውቀት የሚማረው ሰው ይጠቀምበታል፤ በእውቀት ሸሪዓን መጠበቅ ይገኝበታል፤ በእውቀት ፍጡራን ባጠቃላይ ይጠቀማሉ። እውቀት አዳራሽና አጠቃላይ ነው። በህይወት እያለህ ያሉትም ይሁኑ ከሞትክ በኋላ ያሉትም ትተህ ያለፍከው እውቀትህን ይቀስማሉ።
- መልካም ልጆችን በማነፅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በመጪው አለም ወላጆቻቸውን የሚጠቅሙት እነርሱ ናቸውና። ከመልካም ልጆች ጥቅም መካከል ለወላጆቻቸው የሚያደርጉት ዱዓ አንዱ ነው።
- ወላጆች ከሞቱ በኋላ ለነርሱ በጎ በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህ እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ ልጅም ጭምር የሚጠቀምበት በጎ ስራ ነው።
- ከልጅ ውጪ ቢሆን ራሱ ለሞተ ሰው ዱዓ ማድረግ ሟችን ይጠቅማል። ነገር ግን ተለይቶ ልጅ የተጠቀሰው አብዛኛው ጊዜ እስኪሞት ድረስ ሳያቋርጥ ለአንድ ሰው ዱዓ ሊያደርግ የሚችለው ልጅ ስለሆነ ነው።