/ ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።

ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።"
ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለተበዳሪ የእዳ መክፈያ ጊዜውን ያዘገየለት ወይም ያለበትን እዳ ከሱ ላይ ይቅር ያለ ምንዳው፦ የትንሳኤ ቀን ፀሀይ ወደ ሰዎች አናት ቀርባ ሀሩሯ በነሱ ላይ በሚበረታበት ወቅት አላህ ከዐርሹ ስር እንደሚያስጠልላቸው ተናገሩ። አላህ ያስጠለለው ሰው ካልሆነ በስተቀር አንድም ሰው ጥላ አያገኝም።

Hadeeth benefits

  1. ለአላህ ባሮች ነገሮችን የማቅለል ትሩፋቱ፤ እሱም ከትንሳኤ ቀን መከራዎች የመዳኛ ምክንያት ነው።
  2. ምንዳ የሚሰጠን በስራችን ልክ ነው።