- እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት የገንዘብ አይነቶች አምስት ናቸው: ወርቅ፣ ብር፣ ስንዴ፣ ገብስና ተምር ናቸው። ወርቅን በወርቅ እንደመገበያየት አይነቱ ግብይቱ ተመሳሳይ አይነቶችን በመለዋወጥ ከሆነ ግብይቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሁለት መስፈርቶች ሊሟሉ ይገባል: በውሉ ስፍራ ላይ መለዋወጥና ሚዛኑም መመሳሰል ይገባዋል። ይህ ካልሆነ ግን ግብይቱ የማበላለጥ አራጣ ይሆናል። በስንዴ ብር መለዋወጥን ይመስል ግብይቱ የሚካሄደው በተለያዩ የገንዘብ አይነቶች ከሆነ ግን ግብይቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንድ መስፈርት ነው ያለው: እርሱም በውሉ ስፍራ ዋጋውን መቀባበል ነው። ያለበለዚያ ግን የማዘግየት አራጣ ይሆናል።
- የውሉ ስፍራ በማለት የተፈለገበት: ተቀምጠውም ሆነ፣ እየሄዱም ሆነ፣ እየጋለቡም ሆነ የመገበያያው ስፍራውን ነው። ከግብይይቱ ሲለያዩ በማለት የተፈለገው ደግሞ በተለምዶ ተገበያዮች በመካከላቸው ተለያዩ ተብሎ የሚታሰበው ሲከሰት ማለት ነው።
- ሐዲሡ ውስጥ ያለው ክልከላ ለመገበያያ የተበጀውንም ይሁን ሌሎቹን የወርቅና የብር አይነቶችን ባጠቃላይ ያካትታል።
- በዚህ ዘመን የምንጠቀመው መገበያያ ገንዘብም ምንዛሬም በወርቅና ብር ላይ ግዴታ የሆነው ነገር እርሱም ላይ ግዴታ ይሆናል። ማለትም አንድን ጥሬ ገንዘብ በሌላ ጥሬ ገንዘብ መመንዘር ከፈለግክ ሪያልን በዲርሃም መመንዘር ይመስል ሁለቱ ወገኖች በተስማማቸው መልኩ ማበላለጥ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን ግብይቱ በተፈፀመበት ስፍራ (ወዲያውኑ) መለዋወጥ ግዴታ ነው። ያለበለዚያ ስምምነታቸውም ተቀባይነት አይኖረውም፤ ግብይታቸውም ክልክል የሆነው አራጣዊ ግብይት ይሆናል።
- አራጣዊ ግብይት አይፈቀድም። ሁለቱ ወገኖች ቢስማሙ እንኳ ስምምነቱም ተቀባይነት የለውም። እስልምና ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ ሐቁን ችላ ቢልም እንኳ ሐቁን ይጠብቅለታልና።
- የቻለ ሰው መጥፎን ነገር መከልከልና ማውገዝ እንዳለበት እንረዳለን።
- ዑመር ቢን አልኸጧብ እንዳደረጉት መጥፎን በምናወግዝበት ወቅት ማስረጃን መጥቀስ እንደሚገባ እንረዳለን።