- የረመዷንን ዘካተል ፊጥር ለህፃን፣ ለትልቅ፣ ለነፃ፣ ለባሪያ ማውጣቱ ግዴታ ነው። እንዲያወጣ የሚጠየቀውም የቤት ሃላፊውና አስተዳዳሪው ነው። ሰውዬው ለራሱ፣ ለልጆቹና ቀለባቸው ግዴታ ለሆነበት አካላት የማውጣት ግዴታ አለበት።
- ዘካተል ፊጥርን ለፅንስ ማውጣት ግዴታ አይደለም። ይልቁንም ተወዳጅ ነው።
- ለዘካተል ፊጥር የሚወጣው ነገር ምንነቱ መገለፁ፤ እርሱም የተለመደውን የሰዉ ቀለብ ነው።
- ዘካተል ፊጥርን ከዒድ ሶላት በፊት ማውጣት ግዴታ ነው። በላጩ የዒድ ንጋት ላይ ማውጣት ነው። ይሁን እንጂ ከዒዱ ቀን አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ማውጣትም ይፈቀዳል።