- የፆም ትሩፋትን እንረዳለን። ፆም በዱንያ ፆመኛውን ከስሜት ይጠብቀዋል። በመጪው አለም ደግሞ ከእሳት ቅጣት ይጠብቀዋል።
- ከፆም ስነ ስርዓቶች መካከል ፀያፍ ንግግርና ጫጫታን መተው፤ ሰው በሚያውከን ሰአት መታገስ፣ የነርሱን መጥፎ ተግባር አፀፋ በትእግስትና በመልካም መመለስ ይጠቀሳሉ።
- ፆመኛ ወይም አንድ ባሪያ አምልኮው በመጠናቀቁና በመሙላቱ ምክንያት መደሰቱ በመጪው አለም ከሚያገኘው ምንዳ ምንም አያጎድልበትም።
- የተሟላ ደስታ የሚገኘው አላህን በመገናኘት ነው። ይህም ታጋሾችና ፆመኞች ምንዳቸውን ያለቁጥር በሚመነዱበት ወቅት ማለት ነው።
- አስፈላጊና ጠቃሚ ሆኖ በሚገኝበት ወቅት አምልኮ ላይ መሆንን ለሰዎች ማሳወቅ ይዩልኝ አያስብልም። (እኔ ፆመኛ) ነኝ ይበል ስላሉ።
- አንድ ሰው የተሟላ ፆም ፆመ የሚባለው አካላቱ ወንጀል ከመፈፀም የቆጠበ ጊዜ፤ ምላሱ ከውሸት፣ ከፀያፍ ንግግርና የቅጥፈት ንግግር ከመናገር ዝም ያለ ጊዜ፤ ሆዱም ከምግብና መጠጥ የተከለከለ ጊዜ ነው።
- ከጫጫታ፣ ከክርክርና ከመጮህ በአፅንዖት መከልከሉ ለፆመኛ ይበልጥ የበረታ ይሁን እንጂ ፆመኛ ያልሆነም ሰው ከነዚህ ተግባራት ተከልክሏል።
- ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከጌታቸው ከሚያወሩት ሐዲሥ መካከል ነው። "ሐዲሠል ቁድስ" ወይም "ሐዲሠል ኢላሂይ" በመባልም ይጠራል። ይህም ቃሉም መልዕክቱም ከአላህ ቢሆንም ቁርአን ከሌሎች የተለየበት የሆኑ ‐ማለትም ማንበቡ ብቻ አምልኮ መሆኑ፣ ለማንበብ ዉዱእ ማስፈለጉ፣ አላህ የርሱን አምሳያ አምጡ ብሎ መገዳደሩ፣ ተአምራዊነትና ሌሎችም‐ የቁርአን መገለጫዎች የሌሉት ነው።