- በሰዎች እጅ ያሉ ገንዘቦች እሱ በደነገገላቸው መንገድ እንዲያወጡትና ያለአግባብ ከመገልገል ይርቁ ዘንድ ሰዎችን ምትክ ያደረገበት የአሏህ ገንዘቡ ነው። ይህም መሪዎችንም ሆነ ሌሎችንም አጠቃላይ ሰዎችን የሚጠቀልል ነው።
- ሸሪዓ በማህበረሰቡ ገንዘብ ዙሪያ ጥብቅ መሆኑን እንረዳለን። ከገንዘብ በጥቂቱም ቢሆን የተሾመ ሰው የትንሳኤ ቀን ስለገንዘቡ አሰባሰብም ሆነ ስለአወጣጡ ይተሳሰባል።
- የራሱንም ገንዘብ ሆነ የሌላውን ገንዘብ ሸሪዓዊ ባልሆነ መልኩ የሚገለገልም በዚህ ዛቻ ይካተታል።