- አላህ ዐዘ ወጀል በዛቱ፣ በባህሪው፣ በድርጊቱና በህግጋቶቹ ምሉዕ መሆኑን እንረዳለን።
- ስራን ለአላህ ዐዘ ወጀል በማጥራት ላይና ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- "አላህ መልክተኞችን ባዘዘው ነገር አማኞችንም አዟል።" ከሚለው የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ንግግር ለስራ የሚያነሳሳን አገላለፅ መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን። አንድ አማኝ ይህ ነገር መልክተኞችም የታዘዙት ነገር መሆኑን ሲያውቅ ለመተግበር ይበራታልም ይነሳሳልም።
- ዱዓን ተቀባይነት ከሚያሳጡ ነገሮች መካከል ሐራም መብላት አንዱ ነው።
- ዱዓ ተቀባይነት እንዲኖረው ከሚያደርጉ ሰበቦች መካከል አምስት ነገሮች ይገኛሉ: አንደኛ: ጉዞ ማርዘም ነው። በጉዞ ውስጥ ዱዓ ተቀባይነት ከሚያስገኙ ሰበቦች መካከል ትልቁ ሰበብ የሆነው ስብር (በጣም መተናነስን) ማለትን አቅፏልና። ሁለተኛ: በጭንቅ ሁኔታ ላይ መሆን። ሶስተኛ: እጆችን ወደ ሰማይ መዘርጋት። አራተኛ: የአላህን ጌትነት ደጋግሞ በማውሳት አላህ ላይ ችክ ማለት ሲሆን ይህም ዱዓ ተቀባይነት ያስገኛል ከሚባሉት መካከል ትልቁ ሰበብ ነው። አምስተኛ: ምግብና መጠጥን ማሳመር ናቸው።
- መልካምና ሐላል መብላት ለመልካም ስራ ከሚያግዙ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።
- ቃዲ እንዲህ ብለዋል: መልካም (ጥሩ) ማለት የቆሻሻ ተቃራኒ ነው። በዚህ ባህሪ የተገለፀው አሏህ ሲሆን የሚፈለገው እርሱ ከጉድለቶች የፀዳ መሆኑንና ከእንከኖች የጠራ መሆኑን ነው። የተገለፀው በጥቅሉ ባሪያ ሲሆን ደግሞ ከውዳቂ ስነምግባርና ከፀያፍ ተግባራት የፀዳ መሆኑንና ከዚህ ተቃራኒ የሆነን ማንነት የተላበሰ መሆኑን የሚገልፅ ነው። ገንዘብ ሲገለፅበት ደግሞ ገንዘቡ ሐላል መሆኑንና ከምርጥ ገንዘብ መካከል እንደሆነ የሚገልፅ ነው።