- በአላህ መንገድ መስጠትና መመፅወት መበረታታቱን እንረዳለን።
- መልካም በሆኑ መንገዶች ላይ ወጪ ማድረግ ሲሳያችን በረከት እንዲያገኝና እንዲባዛ ከሚያደርጉ እንዲሁም ሰውዬው ያወጣውን ወጪ አላህ እንዲተካለት ከሚያደርጉ ትልልቅ ምክንያቶች መካከል ነው።
- ይህ ሐዲሥ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው ከሚያስተላልፉት ሐዲሥ መካከል አንዱ ነው። ሐዲሠል ቁድሲይ ወይም ሐዲሠል ኢላሂይ በመባል ይጠራል። ቃሉም ሀሳቡም ከአላህ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌሎች የተለየበት የሆኑ በማንበቡ (በየፊደላቱ ሐሰና የሚያስገኘውን) አምልኮን መፈፀም፣ እሱን ለማንበብ ውዱእ ማድረግና አምሳያውን ማንም እንደማያመጣ መነገሩ፣ ተአምራዊነቱና ከዚህም ውጪ ያሉ የቁርአን መለዮዎችን አልያዘም።