- ዝሙት ላይ የመውደቂያን መዳረሻ ለመዝጋት ወደ ባዳ ሴቶች ከመግባትና ከነርሱ ጋር ለብቻ ከማሳለፍ መከልከሉን እንረዳለን።
- ይህ ክልከላ የሴቷ ቅርብ ዘመዶች ያልሆኑን የባል ወንድምንና ቅርብ ዘመዶቹን ጨምሮ ባዳ ወንዶችን ባጠቃላይ የሚጠቀልል ነው። (ባል በሌለበት) መግባቱ ብቻ ከርሷ ጋር መገለልን ማስፈረዱ የማይቀር ጉዳይ ነው።
- መጥፎ ነገር ላይ መውደቅን በመፍራት ብዙሃን ስህተት ላይ የሚወድቁበትን ስፍራ መራቅ ይገባል።
- ነወዊ እንዲህ ብለዋል: «የቋንቋ ምሁራን ባጠቃላይ እንደተስማሙት "አሕማእ" ማለት የባል ቅርብ ዘመዶች ናቸው። አባቱ፣ አጎቱ፣ ወንድሙ፣ የወንድሙ ልጅ፣ የአጎቱ ልጅና የመሳሰሉት ማለት ነው። "አኽታን" ማለት ደግሞ የሚስት ቅርብ ዘመዶች ናቸው። "አስሃር" የሚለው ቃል ደግሞ ለሁለቱም የሚውል ስም ነው።»
- የባል ዘመድ ከሞት ጋር አመሳስለው የመግለፃቸው ምስጢር:- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ዐረቦች የሚጠሉትን ነገር በሞት ይመስሉታል። የመመሳሰሉም መልክ ከባል ዘመድ ጋር ወንጀል ከተፈፀመ በዲን በኩል እንደሞት ነው፤ ወንጀል ከተፈፀመም ከባል ዘመድ ጋር ተገልላ ያሳለፈችው የመወገር ግዴታ ስላለባት ትሞታለች፤ ባል ቅናቱ ለፍቺ ከገፋፋውም ከባሏ መለየቷ ለሴቷ ጥፋት ነው።»