- የወሊይ መኖር ጋብቻው ትክክለኛ እንዲሆን መስፈርት ነው። ያለ ወሊይ ወይም ሴቲቱ ራሷን ብትድር ጋብቻው አይበቃም።
- ወሊይ የሚሆነው ወደ ሴቷ እጅግ ቅርብ ዘመድ የሆነ ወንድ ነው። ከርሱ የቀረበ ወሊይ እያለ ሩቅ የሆነ ወሊይ እሷን ማጋባት አይችልም።
- ወሊይ ለመሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባዋል: - አቅመ አዳምና የአይምሮ ጤነኛ (ሙከለፍ) መሆን፣ ወንድ መሆን፣ የጋብቻን ጥቅም የሚያውቅ አስተዋይ መሆኑ (ቂላቂል አለመሆን) ፣ ወሊዩና ተጋቢዋ ተመሳሳይ እምነት መከተላቸው ነው። እነዚህን ባህሪያቶች ያልተላበሰ የጋብቻን ውል በማሰር ረገድ ለወሊይነት የተገባ አይደለም።