- የሰው ልጅ ተጠያቂነት የሚነሳለት ወይ ግዴታውን ከመፈፀም መንቃት እንዳይችል ባደረገው እንቅልፍ ምክንያት ነው፤ ወይም ከተጠያቂነት እድሜ በማነሱና ልጅ በመሆኑ ምክንያት ነው ፤ ወይም የአይምሮው ተግባር የተምታታበት እብድ በመሆኑ ወይም ወደ እብደት የተጠጋ ስካር ላይ በመሆኑ ምክንያት ነው። ትክክለኛ መለየትንና መረዳት ያልቻለ ሰውና በነዚህ ሶስት ምክንያቶች ሳቢያ ለተጠያቂነት ብቁ ያልሆነ ሰው አላህ ተባረከ ወተዓላ በፍትሃዊነቱ፣ በቻይነቱና ቸርነቱ በአላህ ሐቅ ላይ ከሚያጓድለው ወይም ወሰን ከሚያልፈው ነገር ተጠያቂነቱን አንስቶለታል።
- በነርሱ ላይ ወንጀል አለመፃፉ አንዳንድ ዱንያዊ ፍርዶች ይመለከታቸዋል ከሚለው ጋር አይጣረስም። ለምሳሌ እብድ ቢገል የመገደልና ጉማ የመክፈል ግዴታ የለበትም። በወራሽ ቤተሰቦቹ (የርሱ "ዓቂላ" በሆኑት) ላይ ግን ጉማ የመክፈል ግዴታ አለባቸው።
- ለአቅመ አዳምነት መድረስ ሶስት ምልክቶች አሉት: በህልም ወይም በሌላ ምክንያት የዘር ፈሳሽ ማፍሰስ ወይም የብልት አካባቢ ፀጉር በማብቀል ወይም አስራ አምስት አመት በመሙላት ነው። ሴት ከሆነች አራተኛ ምልክት አላት፤ እርሱም የወር አበባ ማየት ነው።
- ሱብኪ እንዲህ ብለዋል: ጨቅላ በማለት የተፈለገው ህፃን ልጅ ማለት ነው። ሌሎች ዑለሞች ደግሞ: ልጅ እናቱ ሆድ ውስጥ እያለ ፅንስ ይባላል። ሲወለድ ጨቅላ ሲጠነክር ጀምሮ እስከ ሰባት አመቱ ደግሞ ህፃን ይባላል። ከዚያም እስከ አስር አመቱ ለምድ አዙር ይባላል። ከዚያም እስከ አስራ አምስት አመቱ ደግሞ የደረሰ ይባላል። በነዚህ ሁሉ አመታት ውስጥ ባለው እርከን ህፃን ልጅ ከመባል አይወገድም ብለዋል። ይህንም የተነተኑት ሱዩጢይ ናቸው።