- አይንን በመስበር መታዘዙን እንረዳለን።
- ዓይኑ ማየቱ ክልክል ወደ ሆነ ነገር ሳያስበው በድንገት ካረፈ አትኩሮ ከመመልከት መከልከሉን እንረዳለን።
- እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ሶሐቦች ዘንድ ሴቶችን የመመልከት ክልክልነት የተረጋገጠ ጉዳይ እንደነበር ያስረዳናል። የዚህም ማስረጃው ጀሪር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጠየቀው ሳያስበው ዓይኑ ሴት ልጅ ላይ ቢያርፍ ብይኑ አስቦ እንዳየው ነውን? የሚል ነበርና ነው።
- ይህ ሐዲሥ ሸሪዓ ሰዎችን ለሚጠቅም ነገር እንዴት ትኩረት እንደሰጠ ያስረዳናል። ሴትን ልጅ ማየት ዱንያዊና አኺራዊ ጉዳት ስለሚያስከትል ሸሪዓ ሴትን ከመመልከት ከለከለ።
- ሶሐቦች አስቸጋሪ ጥያቄ ሲያጋጥማቸው ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ተመልሰው እንደሚጠይቁ እንረዳለን። ልክ እንደዚሁ ዛሬም ሙስሊሞች አስቸጋሪ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው ወደ ዑለማዎች ተመልሰው መጠየቅ ይገባቸዋል።