/ የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።

የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከልክለዋል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የጭንቅላት ፀጉርን አንዱን ተላጭቶ አንዱን ትቶ ከመቆረጥ ከለከሉ። ክልከላው ልጅም አዋቂም ወንዶችን የሚያጠቃልል ነው። ሴት ግን የጭንቅላት ፀጉሯን መላጨት አይፈቀድላትም።

Hadeeth benefits

  1. ኢስላማዊ ሸሪዐ ለሰው ልጅ አካላዊ መገለጫም ትኩረት መስጠቱን እንረዳለን።