- በወንዶች ላይ ቀጭንና ወፍራም ሐር ክልክል መሆኑንና የለበሰው ላይም ብርቱ ዛቻ እንዳለበት እንረዳለን።
- ቀጭንና ወፍራም ሐር መልበስ ለሴቶች ይፈቀዳል።
- በወንድም ሆነ በሴቶች ላይ በወርቅና ብር ትሪዎችና እቃዎች መብላትና መጠጣት ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
- የሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና አወጋገዝ ጠንከር ያለ መሆኑን እንመለከታለን። የዚህንም ምክንያት ከአንድ ጊዜ በላይ የወርቅና ብር እቃዎችን እንዳይጠቀም መከልከሉና እርሱ ግን አለመቆጠቡ እንደሆነ ገልጿል።