- ሐላልን ሐራም ሐራምን ሐላል ከሚያደርጉ መስፈርቶች በስተቀር ከሁለቱ ጥንዶች መካከል አንዱ ለሌላው ቃል የገባውን መስፈርቶች መሙላት ግዴታ ነው።
- የኒካሕን መስፈርቶች ማሟላት ከሌላ መስፈርቶች የበለጠ ሊሟላ የሚገባው ነው። ምክንያቱም እነዚህ መስፈርቶች ብልትን ሐላል ለማድረግ የሚገቡት ቃል ነውና።
- ኢስላም የጋብቻ መስፈርቶችን እንዲጠበቁ አፅንኦት መስጠቱ ጋብቻ በኢስላም ውስጥ ያለው ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑን ያስረዳል።