- ኡዱሒያ የተደነገገ እንደሆነ እንረዳለን። በዚህም ጉዳይ ዑለሞች ባጠቃላይ ተስማምተዋል።
- ኡዱሒያው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያረዱት አይነት መሆኑ በላጭ ነው። ይህም ሲታይ ስለሚያምርና ሞራውና ስጋውም ጣፋጭ ስለሚሆን ነው።
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «በዚህ ሐዲሥ አንድ ሰው ኡዱሒያውን በራሱ ማረድ እንደሚገባና በቂ ምክንያት ሳይኖረው ለማረድ ሰው መወከል እንደሌለበት እንረዳለን። በቂ ምክንያት ካለው ግን ሲታረድ መገኘቱ ይወደድለታል። በርሱ ፋንታ እንዲያርድለት ሙስሊም ሰው ከተካ ያለምንም ልዩነት ይፈቀዳል።
- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «በዚህ ሐዲሥ ውስጥ በማረድ ወቅት ቢስሚላህ ከማለት ጋር አላሁ አክበር ማለት እንደሚወደድ፤ እግርን ደሞ በሚታረደው ቀኝ የአንገቱ ክፍል ላይ ማኖር እንደሚወደድ እንረዳለን። የሚታረደውን የምናስተኛው በግራ ጎኑ በመሆኑ ዑለሞች ተስማምተዋል። ለአራጁ ቢላን በቀኝ እጅ መያዝ፣ በግራ እጁ ደግሞ ጭንቅላቱን መያዝ እንዲቀለው እግሩን በሚታረደው እንስሳ ቀኝ አንገት ላይ ያደርጋል።
- ኡዱሒያ ቀንዳሙን ማረድ እንደሚወደድ እንረዳለን። ቀንድ ከሌለውም ግን ይፈቀዳል።