ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።"
የአማኞች እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህን በማውሳት ላይ እጅግ ጉጉ እንደነበሩና በሁሉም ወቅት፣ ስፍራና ሁኔታ ላይ ሆነውም አላህን ያወሱ እንደነበር ተናገረች።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካምስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል: "ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።"
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአምልኮዎች መካከል ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ እጅግ በላጭ የሆነ አምልኮ አንድም እንደሌለ ገለፁ። ምክንያቱም ዱዓእ የአላህን መብቃቃት፣ የባሪያን ደካማነትና ፈላጊነት እውቅና መስጠትን ውስጡ ይዟልና ነው።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ «ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በ...
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም ወንጀልና በደል ለመፈፀም እንዲገራለት መለመንን የመሰለ ወንጀል ባልሆነ፤ በቅርብ ዘመዱና በልጆቹ ላይ እርግማን መለመንን የመሰለ ዝምድና መቁረጥ ባልሆነ ዱዓእ አላህን የ...
ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች አሉ። በየሁሉም ደረጃዎች...
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመጪው አለም ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች እንዳሉ፤ በየሁሉም ደረጃዎች መካከል የሚገኘው ርቀት በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ያህል ርቀት እንደሆነ፤ ከነዚህ ጀነቶች መካከል ከፍተኛዋ...
ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሠቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ" (አንተ ልቦናን ገለባባ...
አብዛኛው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱዓ በኢስላምና በአምልኮ ላይ መፅናትንና ከጥመት መራቅን አላህን የሚጠይቁበት ነበር። አነስ ቢን ማሊክም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነ...

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካምስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል: "ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።"

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ «ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በዛች ዱዓው ምክንያት አላህ ከሶስት ነገሮች አንዱን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ: ወይ የለመነው በፍጥነት ይሰጠዋል ፤ ወይ ልመናው ለመጪው ዓለም መልካም ምንዳ ማደለቢያ ይሆንለታል፤ ወይም የለመነውን ጉዳይ የሚያክል መጥፎ ነገር ከሱ ዞር ያስደርግለታል። " ሶሀቦችም " ስለዚህ (ዱዓእ) እናብዛ?" አሉ። እሳቸውም "(ዱዓእ ካበዛችሁ) የአላህ ስጦታም እጅግ ይበዛል።" አሏቸው።»

ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች አሉ። በየሁሉም ደረጃዎች መካከል በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ርቀት ያህል አለ። ፊርደውስ የላይኛው ደረጃ ነው። የጀነት ወንዞች የሚመነጩትም ከርሷ ነው። ከላዩዋ ያለውም (ጣሪያዋ) ዐርሽ ነው። አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።"

ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሠቢት ቀልቢ ዐላ ዲኒክ" (አንተ ልቦናን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ! ልቤን በሃይማኖትህ ላይ አፅናት) ማለትን ያበዙ ነበር። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶና ይዘውት በመጡት ሃይማኖት አምነናል። በኛ ላይ የሚፈሩልን ጉዳይ አለ ማለት ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "አዎን ልቦች በአላህ ሁለት ጣቶች መካከል ናቸው። እንደፈለገው ይገለባብጣታል።" አሉኝ።»

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ አስሊሕ ሊ ዲኒለዚ ሁወ ዒስመቱ አምሪ ወአስሊሕ ሊ ዱንያየለቲ ፊሃ መዓሺ፣ ወአስሊሕ ሊ አኺረቲለቲ ፊሃ መዓዲ፣ ወጅዐሊል ሐያተ ዚያደተን ሊ ፊ ኩሊ ኸይር፣ ወጅዐሊል መውተ ራሐተን ሊ ሚን ኩሊ ሸር"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! የነገሮቼ መጠበቂያ የሆነውን ሃይማኖቴን አስተካክልልኝ። በውስጧ ኑሮዬ የሆነውን ዱንያዬንም አስተካክልልኝ። መመለሻዬ የሆነውን የመጨረሻውን አለምም አስተካክልልኝ። ህይወቴን ሁሉንም መልካም ነገር የምጨምርበት አድርገው። ሞቴንም ከሁሉም መጥፎ ነገር የማርፍበት አድርገው።" ማለት ነው።

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚያመሹና በሚያነጉ ጊዜ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይቦዝኑም ነበር። "አላሁም ኢኒ አስአሉከልዓፊያተ ፊድ-ዱንያ ወልአኺረቲ፣ አላሁም ኢኒ አስአሉከል ዐፍወ ወልዓፊየተ ፊ ዲኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፣ አላሁም ስቱር ዐውረቲ -አው ዓውራቲ- ወአሚን ረውዓቲ፣ አሏሁም ሕፈዝኒ ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ፣ ወአዑዙ ቢአዞመቲክ 'አን ኡግታለ ሚን ተሕቲ"» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ በዱንያዬ፣ በመጪው አለሜ፣ በቤተሰቤና ገንዘቤ ይቅርታህንና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ ነውሬን ወይም ነውሮቼን ሸሽግልኝ፣ ከፍርሃቴም ደህንነትን ስጠኝ፤ አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም ጠብቀኝ! ከበታቼ ድንገታዊ ጥቃት ከሚደርስብኝም በልቅናህ እጠበቃለሁ።) ማለት ነው።

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ዱዓ አስተማሯት: "አልላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚነል ኸይሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ፣ ማ ዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነ ሸሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ ማዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም። አላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ኸይሪ ማሰአለከ ዐብዱከ ወነቢዩከ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማዓዘ ቢሂ ዐብዱከ ወነቢዩክ፣ አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ጀነተ ወማ ቀረበ ኢለይሃ ሚን ቀውሊን አው ዓመሊን፣ ወአስአሉከ አንተጅዐለ ኩለ ቀዿኢን ቀደይተሁ ሊ ኸይራ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ሁሉንም እጠይቅሃለሁ፤ ከመጥፎ ነገርም ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ከሁሉም መጥፎ ነገር ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ባሪያህና ነቢይህ የጠየቀህን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፣ ባሪያህና ነቢይህ ከተጠበቁት መጥፎ ነገርም ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ጀነትንና ወደርሷ የሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባር እጠይቅሃለሁ። ከእሳትና ወደርሷ ከሚያቀርቡ ንግግሮችና ተግባሮች ባንተ እጠበቃለሁ። ለኔ የወሰንከውን ሁሉንም ውሳኔዎች መልካም እንድታደርግልኝም እጠይቅሃለሁ።" ማለት ነው።

ዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ልክ ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።"

ከዓባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "በአሏህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖት እና የነብዩ ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት የወደደ ሰው የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል።"

ከሙዓዝ ቢን ጀበል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ : «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ: "ሙዓዝ ሆይ! ወላሂ እኔ እወድሃለሁ።" እንዲህም አሉ "ሙዓዝ ሆይ! ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።)

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሳለ ነው። (ስለዚህም) ዱዓእን አብዙ!"