- የምግብና የመጠጥ ጣዕም ጥፍጥና በአፍ እንደሚቀመሰው ኢማንም በቀልብ የሚቀመስ የሆነ ጥፍጥናና ጣዕም እንዳለው እንረዳለን።
- ሰውነት የምግብና የመጠጥ ጣዕም ጥፍጥና የሚሰማው ጤነኛ ሲሆን ነው። ልክ እንደዚሁ ቀልብ ከአጥማሚ ዝንባሌና ክልክል ስሜቶች በሽታ ሲነፃ የኢማንን ጥፍጥና ያገኛል። ቀልብ ከታመመና ከተጎዳ ግን የኢማንን ጥፍጥና ሳይሆን የሚያገኘው መጥፊያው የሆነ ወንጀልና ዝንባሌ ነው የሚጣፍጠው።
- የሰው ልጅ አንድን ነገር ከወደደና መልካም ካደረገው ነገሮች ይገሩለታል። አንድም ነገሩ አይከብደውም። ከርሱ በሚመጣ ነገር ባጠቃላይም ይደሰታል። የሚያስደስተው ነገር ነፀብራቅ ቀልቡን ይቀላቀለዋል። ልክ እንደዚሁ አንድ አማኝ ኢማን ቀልቡ ውስጥ የገባ ጊዜ ጌታውን መታዘዝ ይገራለታል፣ ነፍሱም በዚህ ትደሰታለች፣ እርሷን ማከምም አይከብደውም።
- ኢብኑል ቀዪም እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ በአላህ ጌትነትና ተመላኪነት መውደድን፣ በመልክተኛውና ለርሳቸው በመታዘዝ መውደድን፣ በሃይማኖቱና ለርሱ እጅ መስጠቱን መውደድን አካቷል።»