- መልክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል እነዚህን ቃላቶች መጠባበቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
- የሰው ልጅ የሃይማኖቱን ደህንነት አላህን እንዲጠይቅ እንደታዘዘው ሁሉ ለዓለማዊ ጉዳዩም እንዲጠይቅ ታዟል።
- ጢቢ እንዲህ ብለዋል: «ስድስቱን አቅጣጫዎች ማጠቃለላቸው የመከራዎች መምጣት በነርሱ በኩል ስለሆነ ነው። የታች አቅጣጫን አበክረው የጠቀሱት ከታች የሚመጣ መከራ አዋራጅ ስለሆነ ነው።»
- ንጋት ላይ አዝካሮችን ለመቅራት በላጩ ወቅት: ጎህ ከወጣ ጀምሮ የቀኑ መጀመሪያ ላይ ፀሃይ እስክትወጣ ድረስና ከዐስር በኋላ ፀሃይ እስክትገባ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላም ቢል ማለትም ረፋዱ ከፍ ካለ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከዙህር በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከመጝሪብ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ይህም የዚክር ወቅት ነውና።
- ዚክሩ መባል ያለበት በተለየ ወቅት እንደሆነ ማስረጃ ከጠቆመ የሱረቱል በቀራ መጨረሻ ሁለት አንቀጾችን ምሽት ላይ መቅራትን ይመስል ፀሃይ ከገባ በኋላ ምሽት ላይ ነው የሚፈፀመው።