- ሰውን ለአላህ ብለን እንደምንወደው መንገር የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
- በየሁሉም ግዴታና ሱንና ሶላቶች መጨረሻ ላይ ይህን ዱዓ ማድረግ መወደዱን እንረዳለን።
- በነዚህ ጥቂት የዱዓ ቃላት ውስጥ ዱንያዊም አኺራዊም ፍላጎቶች አሉ።
- ለአላህ ብሎ ከመውደድ ጥቅሞች መካከል በእውነት ላይ አደራ መባባል፣ መመካከር፣ በበጎና አላህን በመፍራት ላይ መተጋገዝ ይገኛሉ።
- ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "አላህን ማውሳት የልብ መስፋት መግቢያ ነው። አላህን ማመስገን ደግሞ ተቀባይነት ላለው ፀጋ የሚያዳርስ ነው። አምልኮን ከማሳመር ተፈላጊው ጉዳይ ከአላህ ከሚያዘናጉ ነገሮች መለያየቱ ነው።"