- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓኢሻን እንዳስተማሯት አንድ ሰው ለቤተሰቦቹ ጠቃሚ የሆኑን የዲንና የዱንያ ጉዳዮችን ማስተማር እንደሚገባው እንረዳለን።
- ለአንድ ሙስሊም በላጩ ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የመጡ ዱዓዎችን መሸምደድ ነው። ይህም ጠቅላይ ከሆኑ ዱዓዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ነው።
- ዑለማዎች ስለዚህ ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል: ይህ ሐዲሥ መልካምን በመጠየቅና ከመጥፎ በመጠበቅ ረገድ ጠቅላይ ሐዲሥ ነው። ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተሰጣቸው ጠቅላይ ንግግር መካከልም ነው።
- ከአላህ እዝነት ቀጥሎ ጀነት ከሚያስገቡ ምክንያቶች መካከል መልካም ተግባራትና ንግግሮች ይጠቀሳሉ።