- የሙስሊም ዱዓ የማትመለስ ተቀባይነት ያላት ናት። ነገር ግን ይህ መስፈርቶቿና ስነስርዓቷ የተሟላ ጊዜ ነው። ስለዚህም አንድ ባሪያ አብዝቶ ዱዓ ማድረግ እንጂ የዱዓውን ውጤት በፍጥነት ለማግኘት መቸኮል የለበትም።
- የዱዓ ተቀባይነት ማግኘት የፈለግነውን በማግኘት ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። በዱዓው አማካይነት ወንጀሉን ሊምረው ወይም መጪው ዓለም ላይ ሊያደልብለትም ይችላልና።
- ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል: "ችክ ብሎ ዱዓ ማድረግ፣ በአላህ ላይ ጥሩ እሳቤን ማሳደርና ተስፋ አለመቁረጥ ዱዓ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ከሚያደርጉ ትላልቅ ምክንያቶች መካከል ናቸው። ስለዚህም ሰውዬው ዱዓውን ችክ ብሎ ሊያደርግ፤ በአላህ ላይ ያለው እሳቤን ሊያሳምር፤ አላህ ጥበበኛና አዋቂ እንደሆነ በማወቅ ለአንዳች ጥበብ ሲባል ዱዓውን መቀበልን ሊያፈጥን ለአንዳች ጥበብም ዱዓውን መቀበሉን ሊያዘገይ እንደሚችል መረዳት ይገባል። አላህ ጠያቂ ከጠየቀው የተሻለ ነገርም ይሰጣል።"