- የጀነት ነዋሪዎች በደረጃ እንደሚበላለጡና ይህም በኢማንና በመልካም ስራዎቻቸው ልክ እንደሆነ እንረዳለን።
- አላህን ከጀነት ሁሉ ላእላይ የሆነችውን ፊርደውስ እንድንጠይቀው መነሳሳቱን እንረዳለን።
- ፊርደውስ የጀነት ላይኛዋና በላጯ እንደሆነች እንረዳለን።
- ሙስሊም የሆነ ሰው ከፍ ያለ አላማ ሊኖረው እንደሚገባና አላህ ዘንድ የላቀ የሆነንና በላጭ የሆነን ደረጃ ለማግኘት መልፋትና መጣር እንደሚገባው እንረዳለን።
- ጀነት አራት ወንዞች አሏት: እነርሱም: የውሃ፣ የወተት፣ ወይን ጠጅና የማር ናቸው። እነዚህም በዚህ የአላህ ንግግር ውስጥ በቁርአን ተጠቅሰዋል። {የዚያች ጥንቁቆች ተስፋ የተሰጧት ጀነት ምሳሌ በውስጧ ሽታውን ከማይለውጥ ውሃ ወንዞች፣ ጣዕሙ ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች፣ ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከሆነች የወይን ጠጅም ወንዞች፣ ከተነጠረ ማርም ወንዞች አልሉባት።} [ሙሐመድ: 15]