- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጌታቸው ያላቸው መዋደቅና መተናነስን እንዲሁም ኡመታቸውም ይህንን ጥያቄ እንዲጠይቁ መጠቆማቸውን እንረዳለን።
- በኢስላም ላይ የመፅናትና ቀጥ የማለት አንገብጋቢነቱን እንረዳለን። ዋናው ቦታ የሚሰጠውም ፍፃሜያችን ነው።
- አንድ ባሪያ በኢስላም ላይ መፅናትን ከአላህ ከመፈለግ ለአይን ጨረፍታ ያህል እንኳ አይብቃቃም።
- ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተከትለን ይህንን ዱዓ በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- በእስልምና ላይ መፅናት አንድ ባሪያ ሊለፋለት የሚገባና በርሱም ጌታውን ሊያመሰግንበት የሚገባ ትልቁ ፀጋ ነው።