ከጃቢር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት፣ በመ...
ዑለሞችን ለመወዳደርና ለመፎካከር፣ እኔ እንደናንተው ዓሊም ነኝ የሚለውን ለማሳየት ወይም ቂሎችንና ደካማ ግንዛቤ ያላቸውን ልትሟገቱና ልታናግሩ ወይም በመድረኮች ግንባር ቀደም ለመሆንና ከሌላው ቅድሚያ እንዲሰጠው በማለም ዕውቀት ከመፈለግ ነ...
ከዑስማን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።"
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሙስሊሞች መካከል በላጩና አላህ ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ቁርአን ማንበብን፣ መሸምደድን፣ ማሳመርን፣ መገንዘብንና ማብራራትን የተማረና እርሱ ዘንድ ያለውን የቁርአን እውቀት ከመተግበሩም ጋር ለሌላው ያስተማረ...
አቢ ዐብዲረሕማን አስሱለሚይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ አሉ፦ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰሐቦች መካከል ቁርኣን ያስተምረን የነበረ አንድ ሰሐባ "ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስ...
ሰሐቦች -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ይቀስሙ ነበር። በቀሰሙት አስር አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀት እስኪረዱና እሱን ሳይተገብሩ ወደ ሌ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት...
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማንኛውም ከአላህ መጽሐፍ አንድ ፊደል የሚቀራ ሙስሊም ለርሱ ምንዳ እንዳለውና አንዱ ምንዳ ደግሞ ለርሱ በአምሳያው እስከ አስር ድረስ እንደሚባዛለት ተናገሩ። ከዚያም ይህንን ({አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደ...
ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እን...
ቁርኣንን ለሚያነብ፣ ቁርኣን ውስጥ ባለው ለሚሰራ፣ በቃሉ መሸምደድንም ሆነ አሳምሮ ማንበብን አጥብቆ የያዘ ጀነት በሚገባ ጊዜ "ቁርኣንን አንብብ! በዚህም ሰበብ የጀነት ደረጃዎችን ውጣ! ቁርኣንን በስክነትና እርጋታ ዱንያ ላይ ታነበው እንደ...

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት፣ በመድረኮች ላይ ቅድሚያ እንድትመረጡበት በማለም እንዳትቀስሙ። ይህን የፈፀመ (ለርሱ) እሳት አለው እሳት አለው።"

ከዑስማን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።"

አቢ ዐብዲረሕማን አስሱለሚይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ አሉ፦ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰሐቦች መካከል ቁርኣን ያስተምረን የነበረ አንድ ሰሐባ "ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር። በዚህም "ዕውቀትንም ተግባርንም ተማርን" አሉ።" ብሎ ነገረን።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።) (ይሄንን ስል) {አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።'"

ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።"

አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?" እኛም "አዎን" አልን። እሳቸውም "አንዳችሁ በሰላቱ ውስጥ የሚያነባቸው ሶስት አንቀፆች ከሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎች ለሱ የተሻሉ ናቸው።" አሉ።

ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።"

ኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው- እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ውስጥ ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። " እርሳቸውም በድጋሚ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።

ከአቢ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።"

ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ሰው ከደጃል ይጠበቃል።" በሌላ ዘገባ "ከሱረቱል ከህፍ መጨረሻ አስር አንቀጾች… "

ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: 'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።' ከዚያም {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"} [ጋፊር: 60] የሚለውን አነበቡ።"