- የሱረቱል ከህፍ ትሩፋት መገለፁን እንረዳለን። ይህም መክፈቻዎቿ ወይም መጨረሻዎቿ ከደጃል ፈተና መጠበቃቸው ነው።
- የደጃል ጉዳይ መነገሩና ከርሱ መጠበቂያም መነገሩን እንረዳለን።
- ሱረቱል ከህፍን ሙሉውን በቃል በመሸምደድ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህ ካቃተው ግን ከመጀመሪያውና ከመጨረሻው አስር አንቀጾችን ይሸምድድ።
- ስለዚህ ምክንያትም ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል: «በምክንያቱ ዙሪያ አስሩ አንቀጾች የዋሻው ሰዎች ታሪክ ውስጥ ያሉ ተአምራትን ስላካተቱ ነው። ቆም ብሎ ስለነሱ ያስተነተነ ሰው የደጃል ጉዳይ እንግዳ አይሆንበትምም አያስደነግጠውምም። ስለዚህ በርሱ ፈተና ውስጥ አይወድቁም ተብሏል። {ከርሱ ዘንድ የሆነን ብርቱ ቅጣት ሊያስፈራራበት} የሚለው የቁርአን አንቀፅ ስላለበት መከራና ችግርን ከርሱ ዘንድ ብቻ እንደሆነ መገደቡን በመያዝ ነውም ተብሏል። ይህም ደጃል አምላክነትንና የበላይነትን ከመሞገቱ ጋር ፈተናው ታላቅ መሆኑን የሚገጥም ነው። ስለዚህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የደጃልን ጉዳይ አከበዱት፤ ከርሱም አስጠነቀቁ፤ ከፈተናውም ተጠበቁ። ስለዚህ የሐዲሡ ሀሳብ የሚሆነው እነዚህን አስር አንቀጾች ያነበበ፣ ያስተነተነ፣ በየትርጉሙ ቆም እያለ ያገናዘበ ሰው ደጃልን ይጠነቀቃልም። ከርሱም ደህና ይሆናል ማለት ነው።»