/ ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'

ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'

ከአነስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'"
ቡኻሪ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ዑመር -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ነገርን ንግግርም ይሁን ድርጊት የግድ መቸጋገር ሳያስፈልግ መቸገር ያለበትን ነገር ከመጠቀም እንደከለከሏቸው ተናገሩ።

Hadeeth benefits

  1. ከተከለከሉት ከአቅም በላይ መጣጣር ውስጥ : - ጥያቄ ማብዛት ወይም በርሱ እውቀት በሌለው ነገር ያለአቅሙ መጣጣር ወይም አላህ ያሰፋው ጉዳዩ ላይ ማካበድ ይጠቀሳሉ።
  2. ሙስሊም የሆነ ሰው በንግግሩ፣ በተግባሩ፣ በአመጋገቡ፣ በአጠጣጡና በማንኛውም ሁኔታው ገራገርነትንና አለማካበድን ለነፍሱ ማለማመድ ይገባዋል።
  3. ኢስላም ገር እምነት መሆኑን እንረዳለን።