- በእምነት ካልሆነ በቀር ጀነት መግባት እንደሌለ እንረዳለን።
- የትኛውም ሙስሊም ለነፍሱ የሚወደውን ለወንድሙ መውደዱ ከኢማን መሟላት መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው።
- ለሙስሊሞች ሰላምታን ማብዛትና መለዋወጥ በሰዎች መካከል ውዴታንና ደህንነትን ስለሚያሰራጭ ይወደዳል።
- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "በመካከላችሁ" ስላሉ "አሰላሙ ዓለይኩም" ከሙስሊም ጋር ካልሆነ በቀር አይባልም።
- ሰላምታን መለዋወጥ መቆራረጥን፣ መኮራርፍንና መጣላትን ያስወግዳል።
- በሙስሊሞች መካከል የመዋደድን አንገብጋቢነት እንረዳለን። እርሱም ኢማንን ከሚሞሉ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
- በሌላ ሐዲሥ የተሟላው የሰላምታ ይዘት "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ" እንደሆነ መጥቷል። "አስሰላሙ ዐለይኩም" የሚለውም በቂ ነው።