- ሰዎች በኢማን እንደሚበላለጡ እንረዳለን።
- በስራዎች ላይ ጠንካራ መሆን እንደሚወደድ እንረዳለን። ምክንያቱም በደካማነት የማይገኙ ጥቅሞች በጥንካሬ አማካይነት ሊገኙ ይሆናልና።
- የሰው ልጅ በሚጠቅመው ነገር ላይ መጓጓትና የማይጠቅመው ነገርን ደግሞ መተው ይገባዋል።
- አንድ አማኝ በሁሉም ጉዳዮቹ የአላህን እገዛ መፈለጉ ግዴታ ነው። በነፍሱ ላይ ሊመካም አይገባውም።
- የአላህን ውሳኔና ፍርድ ማፅደቅ ሰበቦችን ከመፈፀምና መልካምን ለመፈለግ ከመልፋት ጋር አይጋጭም።
- ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት በመበሳጨት መልኩ "እንዲህ ባደርግ ኖሮ" ማለት መከልከሉንና የአላህን ፍርድና ውሳኔ መቃወም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።