/ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!

በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር!"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ እና መመለሻውም በስራው የሚመነዳበትም በሆነው መጨረሻው ቀን ያመነ ባሪያ ኢማኑ እነዚህን ጉዳዮችን በመፈፀም ላይ እንደሚያነሳሳው ገለፁ: የመጀመሪያው: መልካም መናገር ነው። በዚህ ውስጥ ሱብሓነላህ ማለት፣ ላኢላሃኢለላህ ማለት፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ በተጣሉ ሰዎች መካከል ማስማማት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ይህንን ካልፈፀመ ዝምታን ያዘውትር፣ ክፋቱን ይቆጥብ፣ ምላሱን ይጠብቅ። ሁለተኛ: ጉረቤትን ማክበር፡ ይህም እነሱን ባለማወክና ለነርሱ በጎ በማድረግ ነው። ሶስተኛ: ለመዘየር የመጣን እንግዳ መልካም በማናገር፣ ምግብ በማብላትና ይህን በመሳሰሉት ማክበር ነው።

Hadeeth benefits

  1. በአላህና በመጨረሻው ቀን ማመን ለሁሉም መልካም ነገር መሰረት ነው። መልካም ተግባራትን በመፈፀም ላይም ያነሳሳል።
  2. ከምላስ ወለምታ መከልከሉን ፤
  3. የኢስላም ሃይማኖት የአንድነትና የቸርነት ሃይማኖት መሆኑን ፤
  4. እነዚህ ጉዳዮች ከኢማን ክፍሎችና ምስጉን ከሆኑ ስነስርአቶች መሆናቸውን ፤
  5. ንግግር ማብዛት ወደሚጠላ ወይም ወደተከለከለ ነገር ይጎትታል። ሰላም የሚገኘው ከመልካም ውጪ ባለመናገር እንደሆነ እንረዳለን።