- የኢስላም ምሉዕነት ሌሎች ላይ ቁሳዊም ሆነ ሞራላዊ ጉዳትን ባለማድረስ ካልሆነ በቀር አይረጋገጥም።
- ምላስና እጅን ብቻ በማውሳት መገደቡ በነርሱ ምክንያት የሚደርስ ጉዳትና ጥፋቶች ስለሚበዙ ነው። ምክንያቱም አብዛኞቹ ክፋቶች የሚመነጩት ከሁለቱ ነውና።
- ወንጀልን በመተው ላይና አላህ ያዘዘውን ነገር አጥብቆ በመያዝ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- በላጩ ሙስሊም የሚባለው የአላህን ሐቆችና የሙስሊሞችን ሐቅ የተወጣ ነው።
- ወሰን አላፊነት በንግግር ወይም በተግባር ሊሆን ይችላል።
- የተሟላ ሂጅራ የሚባለው አላህ ክልክል ያደረገውን በመተው ነው።