- በሸሪዓዊ ጥቅሶች ውስጥ ክልክል በመተግበር ወይም ግዴታን በመተው ካልሆነ በቀር ኢማን ውድቅ አይደረግም።
- አካላትን በመጠበቅና ከመጥፎ ተግባራት በመታቀብ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በተለይ ምላስን።
- ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: (እጅግ ተቺና እጅግ ተራጋሚ) በማለት ሁለቱ በተጋኖ ቃል መጠቀሳቸው ትችትና እርግማን የሚገባውን ሰው በትንሹ መተቸትና መርገም የኢማን ሰዎችን በኢማን ከመገለፅ እንደማያጎድልባቸው ያስረዳል።