- ከማመሳሰል (ከደረሰበት በደል) በበዛ መልኩ መበቀል መከልከሉን፤
- አላህ ባሮቹን በአንዳችም የሚጎዳቸው በሆነ ነገር አላዘዛቸውም ፤
- በንግግር ወይም በተግባር ወይም በመተውም ቢሆን አውቆም ይሁን ሳያውቁ መጉዳት መከልከሉ ፤
- ምንዳ በስራው አይነት ነው የሚሰጠው። የጎዳ ሰው አላህ ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀም አላህ ያጨናንቀዋል።
- ከሸሪዐ መርሆዎች መካከል አንዱ: - "ጉዳት መወገድ ይገባዋል።" የሚል ነው። ሸሪዓ በፍፁም ጉዳትን እንደማያፀናና መጉዳትን እንደሚያወግዝ እንረዳለን።