- የቻይነትና ነፍስን በቁጣ ወቅት የመቆጣጠር ትሩፋትን እንረዳለን። ይህ ኢስላም ያነሳሳበት ከሆኑ መልካም ስራዎች መካከል አንዱ ነውና።
- ነፍስን በቁጣ ወቅት መታገል ጠላትን ከመታገልም የበለጠ ከባድ መሆኑን እንረዳለን።
- ጃሂሊዮች ለሀይለኝነት የሰጡትን ትርጓሜ ኢስላም ወደ ክቡር መገለጫ ስነ ምግባር መለወጡን እንረዳለን። ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ የነፍሱን ልጓም የተቆጣጠረ ነውና።
- በግለሰብም ደረጃ ይሁን በማህበረሰብ ደረጃ ጉዳት ከማስከተሉ አኳያ ከቁጣ መራቅ እንደሚገባ እንረዳለን።