/ አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።

አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።

ከሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።"
አቡዳውድ፣ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በሱነኑል ኩብራ ፣ አሕመድ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምእመናን መካከል መስተጋብራቸውን ከሚያጠናክሩና በመካከላቸውም ውዴታን ከሚያሰፍኑ ሰበቦች መካከል አንዱን ጠቀሱ። ይኸውም አንድ ሰው ወንድሙን የሚወደው ከሆነ እንደሚወደው ይንገረው አሉ።

Hadeeth benefits

  1. ለዓለማዊ ጥቅም ሳይሆን ጥርት ባለ መልኩ ለአላህ ብሎ መውደድ ያለውን ደረጃ፤
  2. መዋደዱና መግባባቱ እንዲጨምር ለአላህ ብለው የሚወዱትን እንደሚወዱት መንገር እንደሚበረታታ፤
  3. በምእመናን መካከል መዋደድ መስፋፋቱ ኢማናዊ የሆነውን ወንድማማችነት እንደሚያጠነክርና ማህበረሰቡንም ከመለያየትና ከመበታተን እንደሚታደግ፤