- ኢብኑ ደቂቅ አልዒዲ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ትልቅና የተለያዩ ዕውቀቶችን፣ መርሆችንና ስነስርዓቶችን የጠቀለለ ሐዲሥ ነው። ይህ ሐዲሥ ሙስሊሞችን ጉዳያቸውን በመፈፀምና በተቻለው መጠን በዕውቀት ወይም በገንዘብ ወይም በእገዛ ወይም ጠቃሚን ነገር በመጠቆም ወይም በምክር ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች ሁሉ መጥቀም እንደሚገባ ያስረዳናል።"
- ለተቸገረ ሰው ችግሩን በማቅለል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- ሙስሊምን በማገዝ ላይ መነሳሳቱንና ወንድሙን ባገዘበት ልክም አላህም አጋዡን ሰው እንደሚያግዘው እንረዳለን።
- ሙስሊምን ከመሸሸግ መካከል ነውሩን አለመከታተል አንዱ ነው። ከሰለፎች ከአንዱ እንዲህ ማለቱ ተዘግቧል "ነውር የሌለባቸው ሰዎች አጋጥመውኛል። የሌሎችን ነውር ያወሩ`ለት ግን ሰዎችም የነርሱን ነውር አወሩባቸው። ነውር የነበረባቸው ሰዎችም አጋጥመውኛል። የሰዎችን ነውር ከማውራት የተቆጠቡ`ለት ነውራቸውም ተረሳች።"
- የሰዎችን ነውር መሸሸግ ማለት እነርሱን አለመምከርና እንዲለወጡ አለማድረግ ማለት አይደለም። ይልቁንም ከመሸሸግም ጋር እንለውጠዋለን። ይህም ማበላሸትና ጥመት ላይ በመዘውተሩ መገለጫው እስኪሆን የደረሰውን አይመለከትም። በዚህ ባህሪ የታወቀ ከሆነ ግን የርሱን ነውር መሸሸግ አይወደድም። ይልቁንም የባሰ መዘዝ እንዳይመጣ ስጋት እስከሌለ ድረስ በርሱ ጉዳይ እርምጃ መውሰድ ወደሚችል ሰው እንወስደዋለን። ይህም ለርሱ ነውሩን መሸሸግ በማበላሸቱ ላይ እንዲታለል፤ ሰዎችን ወደ ማወክ እንዲያመራ ስለሚያደርግና ከርሱ ውጪ ያሉ የክፋትና የአመፅ ባለቤቶችንም ስለሚያደፋፍር ነው።
- ዕውቀትን በመፈለግ፣ ቁርአንን በማንበብና በመማማር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: ይህ ሐዲሥ መስጂድ ውስጥ ቁርአንን ለማንበብ መሰብሰብ ያለውን ትሩፋት ይጠቁማል። ... መድረሳ ውስጥ፣ ዛውያና የመሳሰሉት ውስጥ መሰባሰብም ኢን ሻአ አላህ (በአላህ ፈቃድ) ይህን ደረጃ እንደሚያስገኝ ተስፋ እናደርጋለን።
- አላህ ምንዳን ያስቀመጠው በተግባር ነው እንጂ በዘር አይደለም።