- የሰው ልጅ አጥንቶች ተገጣጥመው መሰራታቸውና የነርሱም ደህና መሆን ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎች መካከል እንደሆነ እንረዳለን። ለያንዳንዱ ፀጋ የሚያቀርበው ምስጋና እንዲሞላም ለሁሉም አጥንት መመፅወት አስፈላጊ ነው።
- ይህ የአላህ ፀጋ እንዲዘወትርም ምስጋናን በየቀኑ በማደስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- በየቀኑ ግዴታ ያልሆኑ ስራዎችን በመስራትና ምፅዋት በማድረግ ላይ በመዘውተር መነሳሳቱን እንረዳለን።
- በሰዎች መካከል ማስታረቅ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
- ወንድምን በማገዝ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም ወንድምን ማገዝ ምፅዋት ስለሆነ ነው።
- የጀመዓ ሶላት በመገኘት ላይ፣ ወደርሱ በመሄድ ላይና መስጂድን በዚህ በማሳመር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- ሙስሊሞች የሚያውካቸውንና የሚጎዳቸውን ነገር በማራቅ የሙስሊሞችን መንገድ ማስከበር ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።