- በአላህ የመማል ጉዳይ ትልቅ እንደሆነና አስፈላጊ ካልሆነ በቀር እንደማይማል እንረዳለን።
- ሐራም ስራ መጠኑ ቢበዛ ራሱ በረከቱ በመነሳቱ መልካም ነገር የለውም።
- አልቃሪይ እንዲህ ብለዋል: "የተሰራው በረከት የሚወገደው ወይ ገንዘቡ በሚያጋጥመው ጥፋት ነው፤ ወይም በቅርብ ህይወቱ ለሚጠቅመው ወይም ለመጪው አለም ምንዳ በማያስገኝለት ጉዳይ ወጪ በማድረግ ነው፤ ወይም እርሱ ዘንድ ቢሆንም መጠቀሙን በመነፈግ ነው፤ ወይም የማያመሰግነው ሰው እንዲወርሰው በማድረግ ነው።"
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በንግድ ወቅት መሀላ ማብዛት ክልክል መሆኑን ያስረዳል። መማል ሳያስፈልግ መማል ይጠላልና። በመሃላ ሸቀጥን ማዋደድ ደሞ ጉዳዩን ያብሰዋል። ምንአልባት ገዢ በመሃላው ታግዞ ገዝቶ ሊሆን ይችላልና።"
- መሀላ ማብዛት የኢማንና የተውሒድ ጉድለት ነው። ምክንያቱም መሀላ ማብዛት ወደ ሁለት ነገር ያደርሳል: አንደኛው: መሀላውን ወደ መዘናጋትና ቦታ ወዳለመስጠት ሲሆን፤ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ: ወደ ውሸት ነው። መሀላው የበዛ ሰው በውሸት የመማል እድሉ ሰፊ ነው። ስለዚህም መሀላን መቀነስና አለማብዛት ይገባል። ይህንን በማስመልከትም አላህ እንዲህ ብሏል: {መሀላዎቻችሁን ጠብቁ!} [አልማኢዳህ: 89]