- ባልና ሚስት ካልሆኑ በቀር ሀፍረተ ገላን ከመመልከት መከልከሉን እንረዳለን።
- ኢስላም ማህበረሰቡን በማፅዳትና ለብልሹነት የሚያደርሱ መንገዶችን በመዝጋት ላይ ያለውን ጥረት እንረዳለን።
- እንደ ህክምና ለመሰሉ ጉዳዮች ሀፍረተ ገላን መመልከት አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ ጊዜ መመልከት ይፈቀዳል። ነገር ግን ከስሜት ውጪ በሆነ ሁኔታ መሆን ይገባዋል።
- ሙስሊም ሀፍረተ ገላውን በመሸፈን ላይና የሌላን ሰው ሀፍረተ ገላ ከመመልከት አይኑን ዝቅ በማድረግ ላይ መታዘዙን እንረዳለን።
- ክልከላው ወንዶችን ከወንዶች ጋር፣ ሴቶችን ከሴቶች ጋር ብቻ በመከልከል መገደቡ ማየትና ሀፍረተ ገላን መግለጥ ብዙ ጊዜ ቀለል ተደርጎ የሚታይ ስለሆነ ነው።