/ 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'

'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'"
አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።

ትንታኔ

መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው ቀኑን በመፆምና ሌሊቱን በመቆም የዘወተረ ሰውን ደረጃ እንደሚደርስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ። መልካም ስነምግባር ሲጠቀለል: መልካምን መለገስ፣ ንግግርን ማሳመር፣ ፊትን መፍታት፣ ሰውን ከመጉዳት መቆጠብና የነሱን ክፋት መቻል ነው።

Hadeeth benefits

  1. ኢስላም ስነምግባርን በማጥራትና በማሟላት ላይ ትልቅ ትኩረት መቸሩን እንረዳለን።
  2. አንድ ሰው በመልካም ስነምግባሩ ቀን ምንም ሳያፈጥር የሚፆምና ምንም ሳይደክም ሌሊቱን የሚቆም ሰው ደረጃ ላይ መድረሱ የመልካም ስነምግባርን ትሩፋት ያስረዳናል።
  3. ቀኑን መፆምና ሌሊቱን መቆም ለነፍስ የሚከብዱ ትልልቅ ስራዎች ናቸው። መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው የነርሱን ደረጃ የደረሰውም ነፍሱን በመልካም መስተጋብር ላይ ስለታገለ ነው።