- የላቀውና የተከበረው አላህ በፍጡራኑ ላይ ያለው እዝነትና ርህራሄን፤
- አገዳደልና አስተራረድ ላይ ኢሕሳን የሚባለው ሸሪዐውን የተከተለ (የዋጀ) በሆነ መልኩ ሲፈፀም ነው።
- ሸሪዐ ምሉዕና ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ሲሆን ከዚህም መካከል ለእንስሳት ማዘኑና መራራቱ አንዱ ነው፤
- የሰውን ልጅ ከገደሉ በኋላ ሰውነቱን መቆራረጥ መከልከሉን፤
- እንስሳትን መቅጣት ያለበት ነገር ሁሉ ክልክል መሆኑን ተረድተናል።