/ ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'

ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'

ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መካከል ፀያፍ መናገር ወይም ፀያፍ ድርጊት አይገኝም ነበር። ትዝም አይላቸው። እሳቸው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የላቀ ስነምግባር ባለቤት ነበሩ። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ዘንድ ከናንተ መካከል በላጩ መልካምን በመለገስ፣ ፊቱን በመፍታት፣ ሰውን ከማወክ በመቆጠብና የነሱን ክፋት በመቻል እንዲሁም ሰዎች ጋር ባማረ መልኩ በመኗኗር ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።"

Hadeeth benefits

  1. አንድ አማኝ ከፀያፍ ንግግርና ከመጥፎ ተግባር ሊርቅ እንደሚገባው፤
  2. የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ምሉዕ መሆኑንና ከሳቸው መልካም ስራና ምርጥ ንግግር እንጂ ሌላ እንደማይመነጭ፤
  3. መልካም ስነምግባር የሽቅድድም መድረክ መሆኑን እንረዳለን። የቀደመ ምርጥ አማኝና ኢማኑ የሞላ ይሆናል።