- የፍትህ ትሩፋቱና በሱ ላይ መበረታታቱ፤
- ፍትህ በሰዎች መካከል ያሉ ሁሉንም ፍርድና ኃላፊነትን የሚያካትት ጠቅላይ ቃል ነው። በሚስቶች፣ በልጆችና በሌሎችም መካከል ፍትህ ማስፈን ሳይቀር ፍትሃዊነት ውስጥ ይገባል።
- የትንሳኤ ቀን የፍትሃዊዎች ደረጃ መገለፁን ፤
- የትንሳኤ ቀን የኢማን ባለቤቶች ደረጃ የሚበላለጥ መሆኑን ፤ ሁሉም በስራው ልክ ነውና የሚመነዳው።
- በማነሳሳት ማስተማር ዘይቤ የሚማሩትን ሰዎች ትምህርቱን እንዲቀበሉ የሚያነሳሳ ከሆኑት የማስተማር ዘይቤዎች መካከል መሆኑን እንረዳለን።