- በይፋም ይሁን በድብቅ አላህን ማውሳት ማዘውተር ከትላልቅ መቃረቢያዎችና አላህ ዘንድ እጅግ ጠቃሚ ከሆኑት ነው።
- ሁሉም ስራዎች የተደነገጉት አላህን ማውሳትን ለማቋቋም (ተፈፃሚ ለማድረግ) ነው። አላህ እንዲህ ብሏል: {ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ።} ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል "በአላህ ቤት ዙሪያ ጦዋፍ ማድረግ፣ በሶፋና መርዋ መካከል መሮጥ፣ ጠጠር መወርወር ሁሉ የተደረገው አላህን ማውሳት ለማቋቋም ነው።" አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
- ዒዝ ቢን ዐብዱሰላም (ቀዋዒድ) በሚባለው መጽሐፋቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል "ይህ ሐዲሥ ምንዳ ሁሉም አምልኮዎች ላይ በልፋት ልክ እንደማይመጣ ከሚጠቁሙ ሐዲሦች አንዱ ነው። አንዳንዴ አላህ በትንሽ ስራ በትልቁ ስራ ከሚመነዳው በላይ ይመነዳል። ምንዳ የስራ ደረጃዎች በልቅና በሚበላለጡት ልክ ይበላለጣል።"
- መናዊ "ፈይዱል ቀዲር" በሚባለው መጽሐፋቸው ውስጥ እንዲህ አሉ: ይህ ሐዲሥ የሚተረጎመው ንግግሩ ከቀረበላቸው ሰዎች አንፃር ነው ዚክር በላጭ የሚሆነው በሚል ነው። ነቢዩ ያናገሩት ሰው በውጊያ ብቃቱ እስልምና የሚጠቀምበትን አንበሳ ጀግና ሰው ቢሆን ኖሮ ለርሱ በላጩ ስራ ጂሀድ ይሉት ነበር። ወይም በገንዘቡ ድሀዎች የሚጠቀሙበትን ሀብታም ቢሆን ኖሮ ያናገሩት ለርሱ በላጩ ስራ ሶደቃ ይሉት ነበር። ሐጅ የሚችልን ሰው ያናገሩ ቢሆን ኖሮ ሐጅ ይሉት ነበር። ወይም ወላጆች ያሉትን ቢያናግሩ ኖሮ እነሱን መንከባከብ ይሉት ነበር። ሐዲሦቹ የሚስማሙት በዚህ መንገድ ነው።
- የተሟላው ዚክር ልቦና እያስተነተነው ምላስ የተናገረው ዚክር ነው። ቀጥሎም በልብ ብቻ የተፈፀመ ዚክር ነው ተፈኩርን ይመስል። ቀጥሎ በምላስ ብቻ የተፈፀመ ነው። በሁሉም ግን ኢንሻ አሏህ ምንዳ ይገኝባቸዋል።
- አንድ ሙስሊም ከሁኔታዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ዚክሮች እንደ ንጋትና ምሽት ዚክሮች፣ ወደ መስጂድ፣ ቤት፣ ሽንት ቤት ሲገባና ሲወጣ የሚባሉትን ዚክሮችና ሌሎችንም አዘውትሮ መፈፀሙ አላህን በብዙ ከሚያመወሱት መካከል ያደርገዋል።