- ሱጁድ ላይ ይሄን ዱዓ ማለት ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
- ሚረክ እንዲህ ብለዋል: «በአንድ የነሳኢ ዘገባ ደሞ ይህን ዱዓ ሶላታቸውን አጠናቀው ወደ መኝታቸው ሲወጡ እንደሚሉት ተዘግቧል።»
- አላህን በቁርአንና ሐዲሥ በመጡ ባህርያቱ ማወደስና በስሞቹ ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
- ይህ ሐዲሥ ፈጣሪን ሩኩዕና ሱጁድ ውስጥ ማላቅ እንደሚገባ ያስረዳናል።
- በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ዛት መጠበቅ እንደሚፈቀደው በአላህ ባህሪም መጠበቅ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
- ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ንግግር ውስጥ ረቂቅ ሀሳብ ይገኛል። እርሱም: እርሳቸው ከአላህ ቁጣ በውዴታው፣ ከቅጣቱ ደሞ በይቅርታው ተጠበቁ። ውዴታና ቁጣ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ናቸው። እንዲሁም ይቅር ባይነትና በወንጀል መቅጣትም ተቃራኒ ናቸው። ለርሱ ተነፃፃሪ የሌለውን አላህን ሱብሓነሁ ወተዓላ ሲጠቅሱ ግን ከርሱ በሌላ ሳይሆን በራሱ ተጠበቁ። የዚህም ሀሳብ: ይቅር ባይነቱ የተጠየቀው አላህ ሊመለክና ሊወደስበት ከሚገባው መብቱ ስለማጓደላችን ነው። (በአንተ ላይ አወድሼ አልዘልቅም።) ሲሉ አንተን በሚገባህ ልክ ማወደስ የምችልበት አቅሙ የለኝም ማለታቸው ነው።"