- ሰውዬው በአላህ ፍቃድ ከድንገተኛ መከራ ወይም ከመከረኛ ጦስ ወይም ከመሳሰሉት የተጠበቀ እንዲሆን ንጋት ላይና ምሽት ላይ እነዚህን ዚክሮች ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
- የመጀመሪያዎቹ ቀደምቶች በአላህ ላይ ያላቸው እርግጠኝነትና የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በተናገሩት ላይ ያላቸው እምነት ጠንካራ መሆኑን እንረዳለን።
- ዚክር በንጋትና በምሽት ላይ የመገደቡ ካሉት ጥቅሞች መካከል ከሙስሊም ላይ ዝንጉነትን መቁረጥና ዘውትር እርሱ የአላህ ባሪያ መሆኑን እንዲያስታውስ ማድረግ ይገኝበታል።
- አላህን የሚያወሳው ሰው ካለው ኢኽላስና የቂን (እርግጠኝነት) ጋር ባለው ኢማን፣ መተናነስና ልቡን እንደማቅረቡ ልክ የዚክሩ ተፅዕኖም የተረጋገጠ ይሆናል።