- ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በእውቀት ላይ ያላቸውን ጥረት እንረዳለን። ለዛም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በእውቀት ጉዳይ አብዝተው ይጠይቁ ነበር።
- ስራዎች ጀነት ለመግባት ምክንያት መሆኑን ማወቃቸው የሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ግንዛቤን ያስረዳናል።
- ከሙዐዝ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የመጣው ጥያቄ በርግጥም ትልቅ ጥያቄ ነው። በእውነቱ ይህ ጥያቄ የህይወትና የመኖር ምስጢር ነውና። በዚህ አለም የሚገኝ የአደም ልጅና የጂን ፍጡር ሁሉ ፍፃሜው ወይ ጀነት ወይ እሳት ስለሆነ ይህ ጥያቄ እጅግ ትልቅ ጥያቄ ነው።
- ጀነት መግባት አምስቱን የእስልምና ማዕዘናት መፈፀምን ተከትሎ መሆኑን እንረዳለን። እነርሱም: ሁለቱ የምስክር ቃሎች፣ ሶላት፣ ዘካ፣ ፆምና ሐጅ ናቸው።
- የእስልምና መሰረት፣ ውዱ አላማና ትልቁ ግዴታ አላህን በአምልኮ ብቸኛ አድርጎ መነጠልና በርሱ ላይ አለማጋራት ነው።
- አላህ ለባሮቹ የምንዳና ወንጀል ማስማሪያ ሰበቦችን እንዲሰነቁ የመልካም በሮችን ለነርሱ መክፈቱ የርሱን እዝነት ያስረዳናል።
- ግዴታን ከተወጡ በኋላ በትርፍ ስራዎች ወደ አላህ የመቃረብን ትሩፋት እንረዳለን።
- ሶላት በእስልምና ያለው ደረጃ ድንኳን የሚቆምበት ምሰሶ ለድንኳኑ እንዳለው ደረጃ ያህል ነው። ምሰሶው ሲወድቅ ድንኳኑም እንደሚወድቀው ሁሉ ሶላት ስትወገድም እስልምናው አብሮ ይወገዳል።
- የሰው ልጅ ሃይማኖቱን ከሚጎዳው ነገር ምላሱን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት እንረዳለን።
- ምላስን መቆጠብ፣ መጠበቅና መገደብ የመልካም ነገር ሁሉ መሰረት ነው።