- በንጋትና ምሽት ወቅት ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል አኳያ ይህን ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
- አንድ ባሪያ በሁሉም ሁኔታዎቹና ወቅቶቹ ወደ ጌታው ፈላጊ መሆኑን እንረዳለን።
- ንጋት ላይ አዝካሮችን ለመቅራት በላጩ ወቅት የንጋቱን ጎህ ከወጣችበት ጀምሮ የቀኑ መጀመሪያ ላይ ፀሃይ እስክትወጣ ድረስ፤ የምሽቱን ከዓስር በኋላ ጀምሮ ፀሃይ ከመግባቷ በፊት ድረስ ያለው ወቅት ነው። ከዚህ በኋላ ቢለው ማለትም የንጋቱን ረፋዱ ከፍ ካለ በኋላ ቢለው ይበቃለታል። ከዙህር በኋላ ቢለውም ይበቃለታል። የምሽቱንም ከመጝሪብ በኋላም ቢለው ይህ የዚክር ወቅት ስለሆነ ይበቃለታል።
- "መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" የሚለው ንግግር ከንጋት ጋር የሚያገናኘው ይህ ቃል ሰዎች ከሞቱ በኋላና የትንሳኤ ቀን በሚቀሰቀሱ ጊዜ ያለውን ህያው መደረግና ትልቁን መቀስቀስ ስለሚያስታውሰው ነው። ከእንቅልፉ የሚነቃበት ይህ ቀንም ነፍሶች የሚመለሱበትና ሰዎች የሚበተኑበት፣ አላህ የፈጠረው አዲስ ንጋት የሚተነፍስበት አዲስ መቀስቀስና አዲስ ቀን ነው። ይህም አዲስ ንጋት በአደም ልጅ ላይ ምስክር እንዲሆን፣ ወቅቶቹና ሰአቶቹም የስራዎቻችን ድልብ የሚሆኑበት [ሌላ እድል] ነው።
- "መመለስም ወደ አንተ ነው።" የሚለው ቃል የምሽት ዚክር ላይ ተስማሚ የሆነው፤ ሰዎች ከስራዎቻቸው፣ ለጥቅማቸውና ለኑሯቸው ከተበታተኑ በኋላ ወደ ቤታቸው በሚመለሱ ጊዜ ወደ የማደሪያቸው መጥተው ማረፍን ያዘወትራሉ። ይህም ወደ አላህ ተባረከ ወተዓላ መመለስን ያስታውሳል።